የገንዘብ ሚኒስቴር ከ30 ሺህ ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ግብይት ላይ እገዳ የሚጥለውን የሕግ ማሻሻያ ለፓርላማ አቀረበ
19:59 17.07.2025 (የተሻሻለ: 20:04 17.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየገንዘብ ሚኒስቴር ከ30 ሺህ ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ግብይት ላይ እገዳ የሚጥለውን የሕግ ማሻሻያ ለፓርላማ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የገንዘብ ሚኒስቴር ከ30 ሺህ ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ግብይት ላይ እገዳ የሚጥለውን የሕግ ማሻሻያ ለፓርላማ አቀረበ
ገደቡን ያለፈ ማንኛውም ግብይት በሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ እና ፍቃድ የተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በመደበኛ የባንክ ሂደት እንዲፈፀም ይገደዳል ተብሏል።
ሚኒስቴሩ እርምጃው የመንግሥት አስተዳደርን ለማዘመን እና የግብር አሰባሰብን ለማሻሻል ወሳኝ ነው ብሏል፡፡
በአንድ ቀን ውስጥ የሚደርግ የተከፋፈለ ክፍያ እንደ ነጠላ ግብይት የሚቆጠር ሲሆን ገደቡን የተላለፈ ሰው የተቀበለውን ክፍያ እጥፍ ሊቀጣ እንደሚችል እና ወጪው ከግብር ቅነሳ ውጪ እንደሚሆን በረቂቅ ሕጉ ተቀምጧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X