የአሜሪካ ቀረጥ የቡድን 20 የፋይናንስ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ የሚያካሂዱት ስብሰባ ላይ ተፀዕኖ አያሳድርም ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ ቀረጥ የቡድን 20 የፋይናንስ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ የሚያካሂዱት ስብሰባ ላይ ተፀዕኖ አያሳድርም ተባለ
የአሜሪካ ቀረጥ የቡድን 20 የፋይናንስ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ የሚያካሂዱት ስብሰባ ላይ ተፀዕኖ አያሳድርም ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.07.2025
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ ቀረጥ የቡድን 20 የፋይናንስ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ የሚያካሂዱት ስብሰባ ላይ ተፀዕኖ አያሳድርም ተባለ

የቡድን 20 የፋይናንስ ሚኒስትሮች እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ለሚካሄደው ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ ክዋዙሉ-ናታል ግዛት ዚምባሊ ከተማ ተሰባስበዋል። ተሳታፊዎቹ በደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ፕሬዝዳንትነት ግዜ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

ዋና ዋና ጉዳዮች፦

የከሰሃራ በታች ድንበር-ተሻጋሪ ክፍያዎች፣

የአፍሪካ ልማትና ዕድገት እንቅፋቶች፤

የአየር ንብረት ለውጥ እና ሌሎች ጉዳዮች።

"በትክክለኛው የጋራ አቅማችን ላይ ለመድረስ የምንፈልግ ከሆነ፤ በተለይም አፍሪካን የሚያስጨንቁ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ፣ ልማታዊ እና ማህበራዊ ተግዳሮቶችን በቆራጥነት ለመፍታት ጥረታችንን ማስፋት አለብን" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የፋይናንስ ሚኒስትር ኢኖክ ጎዶንግዋና ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን ለንግድ መጠቀምን የመሳሰሉ "ፀረ-አሜሪካዊ" ናቸው ባለቻቸው ፖሊሲዎች የተነሳ በብሪክስ አባል ሀገራት ላይ ቀረጥ እጥላለሁ ብላ ብታስፈራራም፤ አፍሪካ ክልላዊ ንግድን ለማሳደግ የተዋሃደ የክፍያ ስርዓት ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ተቀማጭ ባንክ ገዥ ሌሰትጃ ክጋኒያጎ ተናግረዋል።

"የአፍሪካ ጉዳዮች ወጥተዋል፤ ሁላችንም ስለእነዚህ ጉዳዮች እየመከርን ነው" ሲሉ ክጋኒያጎ ከስብሰባው ዋዜማ ለዩኬ ሚዲያ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0