ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አመፅ የሚቀሰቅሱ ባለሥልጣናትን በማስጠንቀቅ ገንቢ እርምጃ እንዲከተሉ ጥሪ አቀረቡ

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አመፅ የሚቀሰቅሱ ባለሥልጣናትን በማስጠንቀቅ ገንቢ እርምጃ እንዲከተሉ ጥሪ አቀረቡ
የኬንያ ፕሬዝዳንት መሪዎች ወጣቶችን ከመቀስቀስ እንዲቆጠቡ እና ይልቁንም ሥራ አጥነትን ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንዲደግፉ አሳስበዋል።
ከ500 በላይ ለሚሆኑ የሐይማኖት መሪዎች ንግግር ያደረጉት ሩቶ፤ ተቺዎቻቸው አማራጭ ፖሊሲ እንደሌላቸውና ችግሮችን ከመጋፈጥ ይልቅ መፈክሮች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል፡፡ “ለ2027 የምርጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ፤ በቂ የውጤት ካርድም ይዣለው” ሲሉ አስረግጠዋል፡፡
አስተዳደራቸው አሳክቷል ያሏቸውን ጉዳዮችም ዘርዝረዋል፦
በሁለትዮሽ የሥራ ስምምነቶች አማካኝነት ለ400 ሺህ ወጣቶች የውጭ ሀገራት የሥራ ቅጥር፣
በተመጣጣኝ የቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ስር ለ320 ሺህ ወጣቶች የሀገር ውስጥ ሥራ ፈጠራ፣
በጂቱሜ ላብስ በኩል ለ80 ሺህ ወጣቶች የዲጂታል ሥራ ፈጠራ።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከ900 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድሎች ባይፈጥሩ ኖሮ በቅርቡ የተካሄዱት ተቃውሞዎች በእጅጉ የከፉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ሩቶ ቁልፍ የኢኮኖሚ ውጤቶችንም አንስተዋል፦
የዋጋ ንረት ከ9.6 በመቶ ወደ 3.8 በመቶ ቀንሷል፣
የሽሊንግ ምንዛሬ ባለበት ረግቷል፤ 1 የኬንያ ሽልንግ/ 130$፣
የዶላር ተቀማጭ ከ7 ቢሊየን ዶላር ወደ 10.8 ቢሊየን ዶላር አድጓል፣
የበቆሎ ዋጋ ቀንሷል፤ የቡናና ስኳር ዘርፍ ገቢ ተሻሽሏል።
በትምህርት ዘርፍ መንግሥት 76 ሺህ መምህራንን ቀጥሯል። ተጨማሪ 24 ሺህ አስተማሪዎችን ለመቅጠር እንዳቀደ እና ይህም በኬንያ የምልመላ ታሪክ ትልቁ ቁጥር እንደሆነ ተናግረዋል። በጤና ዘርፍ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማስፋት ቁርጠኛ እንደሆኑ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X