ደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሀገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲነሳ አሳሰበች
18:03 17.07.2025 (የተሻሻለ: 18:14 17.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሀገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲነሳ አሳሰበች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሀገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲነሳ አሳሰበች
"እነዚህ እርምጃዎች ዓላማቸውን አሳክተዋል፤ አሁን ላይ ግን እድገት እና ደህንነታችንን ለማሻሻል የምናደርገውን ሂደት እያደናቀፉ ነው" ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሀገሪቱን ብሔራዊ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሲከፍቱ ተናግረዋል።
ሰላም፣ ደህንነት እና ብሔራዊ አንድነት ቀዳሚ ጉዳዮች ሆነው ይቀጥላሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ2026 ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ሁሉም ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በ2018ቱ የሰላም ስምምነት በድጋሚ መገዛታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል።
"የሰላም በሮች አሁንም ክፍት ናቸው" በማለት ኪር አጽንኦት የሰጡ ሲሆን ታጣቂ ቡድኖች ወደ ሰላም እንዲመጡም አሳስበዋል። ሰላምን የሚመርጡ ሁሉንም ተቃዋሚ ኃይሎች “ልንቀበላቸው እና በአፋጣኝ ወደ ሠራዊቱ ልናዋህዳቸው” ይገባል ብለዋል።
በመንግሥት ጦር እና በአማፂ ኃይሎች መካከል ያለው ውጥረት ባለፈው የካቲት በላይኛው የናይል ግዛት ውስጥ ተባብሶ ቀጥሏል።
ℹ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የደቡብ ሱዳን ማዕቀቦች ኮሚቴ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያየት ተቀምጦ ነበር። ባለሙያዎቹ በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንደቀጠለ እና በሰላም ስምምነቱ ፈራሚ ኃይሎች መካከል ግጭት መኖሩን አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ በ2018 መጀመሪያ የጦር መሳሪያ እገዳውን የጣለ ሲሆን በቀጠለው የመንግሥት እና የተቃዋሚዎች ግጭት ምክንያት ለበርካታ ዓመታት ሲራዘም ቆይቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሀገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲነሳ አሳሰበች

© telegram sputnik_ethiopia
/