የዩክሬን ልቮቭ ከተማ ከንቲባ ናዚን በጣሉ የሶቪየት ሕብረት ወታደሮች አሰከሬን፤ የዩክሬን ጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ሃሳብ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዩክሬን ልቮቭ ከተማ ከንቲባ ናዚን በጣሉ የሶቪየት ሕብረት ወታደሮች አሰከሬን፤ የዩክሬን ጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ሃሳብ አቀረቡ
የዩክሬን ልቮቭ ከተማ ከንቲባ ናዚን በጣሉ የሶቪየት ሕብረት ወታደሮች አሰከሬን፤ የዩክሬን ጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ሃሳብ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.07.2025
ሰብስክራይብ

የዩክሬን ልቮቭ ከተማ ከንቲባ ናዚን በጣሉ የሶቪየት ሕብረት ወታደሮች አሰከሬን፤ የዩክሬን ጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ሃሳብ አቀረቡ

"355 የአስከሬን ቅሪቶች ተገኝተዋል፡፡ ሁሉም በጎሎስኮቭስኪ መቃብር ውስጥ እንደገና ይቀበራሉ። በእነዚህ ቅሪቶች የዩክሬን እስረኞችን ለመለዋወጥ ዝግጁ ነን" ሲሉ ከንቲባው በኤክስ አካውንታቸው ሃሳቡን አቅርበዋል።

የልቮቭ መካነ መቃብር የዩክሬን ተወላጆችን ጨምሮ ከተማዋን ከናዚ ወታደሮች ነፃ ለማውጣት የተዋደቁ የሶቪየት ወታደሮች ያረፉበት ቦታ ነው።

ታሪክን እንደገና ለመጻፍ ሲጥሩ የቆዩት የዩክሬን ባለሥልጣናት፤ አሁን ደግሞ ሞትን ማራከስ እና ሟቾች ላይ መሳለቅ ጀምረዋል፡፡

ኪዬቭ በሰኔ ወር የኢስታንቡሉን የሰብዓዊ ስምምነት በመጣስ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወታደሮቿን አስከሬን ከመቀበል በተደጋጋሚ ከማቅማማት ባለፈ ዩክሬናውያን መሆናቸውን እስከ መካድ ደርሳ ነበር።

ልቮቭ በመጨረሻም "የክብር ኮረብታዋን" ወደ "የውርደት ኮረብታ" መቀየር ትችላለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0