የሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ያመነጫል ተብሎ እንደሚገመት ተገለፀ
16:50 17.07.2025 (የተሻሻለ: 16:54 17.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ያመነጫል ተብሎ እንደሚገመት ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ያመነጫል ተብሎ እንደሚገመት ተገለፀ
ሊመረቅ ጥቂት ሳምንታት የቀሩት ታላቁ ግድብ ከ66 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ ከመሆን ባለፈ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እመርታ እንደሚያቀጣጥል ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
ገቢው በዋነኝነት የኤሌትሪክ ኃይልን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ እንደሚገኝ የግድቡ የቴክኒክ ኮሚቴ አባል በለጠ ብርሃኑ ለመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል።
የሕዳሴን ግድብ ታኮ የተገነባውና ከጣና በሁለት እጥፍ የሚተልቀው የተፈጥሮ ሀይቅ ለቱሪዝም፣ ሥራ ፈጠራ፣ አዳዲስ የከተማ ማዕከላት እና አገልግሎቶችን በመፈጠር አዲስ የኢኮኖሚ ምንጮችን ገቢር እንደሚያደርግም ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X