የአፍሪካ ሀገራት ከአይሲሲ አባልነት ሊወጡ እንደሚገባ ዕውቁ ፓን አፍሪካኒዊና ጠበቃ ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሎክ ኦቲኖ ሉሙምባ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሀገራት ከአይሲሲ አባልነት ሊወጡ እንደሚገባ ዕውቁ ፓን አፍሪካኒዊና ጠበቃ ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሎክ ኦቲኖ ሉሙምባ ተናገሩ

የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር እንዲሁም በሂደት ላይ ያለውን የፊሊፒንሱን ፕሬዝዳንት ዱቴርቴ የሕግ ሂደትን ለአብነት ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ ፍርድ ቤቱ ምዕራባውያን ኃያላን መንግሥታት አፍሪካን በቁጥጥር ስር ለማዋል እያደረጉት ላለው ጥረት መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተዋል።

"ፍርድ ቤቱ እንደ እስራኤል ባሉ ሀገራት ላይ ያለውን ባህሪ ስትመለከት፤ እስራኤል በስስት ልዩ እንክብካቤ ስታገኝ ትመለከታታለህ። ስለዚህ በአጭሩ እንድ ሰው በእርግጠኝነት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ለባለቤቱ ታማኝ ሆኖ በደካማ ሀገራት ላይ እንደሚጮህ ውሻ እያገለገለ ነው ማለት ይችላል። ያለ ጥርጥር እና ያለማመንታት፤ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ከአይሲሲ መውጣት አለባቸው፤ እናም አፍሪካዊ ተቋማትን መፍጠር እንችላለን" ሲሉም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ፕሮፌሰሩ አፍሪካዊያን አሕጉር አቀፍ የሕግ ተቋማትን ከማጠናከር ባለፈ፤ ያለመከሰስ መብት ባሕልን ለመገርሰስ መታገል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0