በኬንያ ክትባት የሚወስዱ ሕፃናት ቁጥር በአስደንጋጭ መጠን ቀነሰ፤ በ2024 133 ሺህ ሕፃናት መደበኛ ክትባቶችን አላገኙም
19:45 16.07.2025 (የተሻሻለ: 19:54 16.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኬንያ ክትባት የሚወስዱ ሕፃናት ቁጥር በአስደንጋጭ መጠን ቀነሰ፤ በ2024 133 ሺህ ሕፃናት መደበኛ ክትባቶችን አላገኙም

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኬንያ ክትባት የሚወስዱ ሕፃናት ቁጥር በአስደንጋጭ መጠን ቀነሰ፤ በ2024 133 ሺህ ሕፃናት መደበኛ ክትባቶችን አላገኙም
የዓለም ጤና ድርጅት እና የተመድ የሕፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ያወጡት አዲስ ሪፖርት እንዳመለከተው፤ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ90 ሺህ ጭማሪ ታይቷል። ኬንያ አሁን በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ዜሮ-ዶዝ ህፃናት (ምንም አይነት ክትባት ወስደው የማያውቁ) 4.7 በመቶ ድርሻ ትይዛለች።
በኬንያ የተስፋፋ የበሽታ መከላከያ ፕሮግራም ስር ከሚሰጡ 14 ክትባቶች ውስጥ አራቱ ብቻ የ90 በመቶ የሽፋን እቅዱን ያሟሉ ሲሆን ይህም ብዙ ሕፃናትን ቅደመ መከላከያ ላላቸው በሽታዎች ተጋላጭ አድርጓቸዋል።
የኩፍኝ-ሩቤላ እና በአፍ የሚሰጡ የፖሊዮ ክትባቶች ከፍተኛ እጥረት ምክንያት 178 ሺህ ሕፃናት የመጀመሪያውን የኩፍኝ ክትባት ሳያገኙ ቀርተዋል።
ምንም እንኳን የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሽፋን በ9-14 ዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ልጃገረዶች የመጀመሪያ መጠን ከ4 በመቶ ወደ 79 በመቶ ከፍተኛ ለውጥ ቢያሳይም፤ ሙሉ ክትባት የወሰዱት 36 በመቶ ብቻ ናቸው።
የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ ተደጋጋሚ የኩፍኝ ክትባት እጥረት እና የአቅርቦት ሰንሰለት ችግሮችን አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X