ኮትዲቯር ብሔራዊ የሕፃናት የወባ ክትባት ዘመቻ አስጀመረች
19:18 16.07.2025 (የተሻሻለ: 19:24 16.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኮትዲቯር ብሔራዊ የሕፃናት የወባ ክትባት ዘመቻ አስጀመረች
ለ10 ቀናት በሚካሄደው ዘመቻ በ115 የጤና አውራጃዎች የሚገኙ 420 ሺህ እድሜያቸው ከ6 እስከ 23 ወር የሆኑ ሕፃናትን ለመከተብ ታቅዷል።
የጤና ሚኒስትሩ ፒየር ንጉ ዲምባ ዘመቻውን "እስከ 2030 ኮትዲቯርን ከወባ ነጻ ለማድረግ ቁልፍ እርምጃ" ሲሉ ገልፀው፤ "ከአንድ ሺህ ሕፃናት 920ቹ በወባ በሽታ መጠቃታቸው እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የትንኞቹ የፀረ-ነፍሳት ማጥፊያ የመቋቋም አቅም ከ25 በመቶ ወደ 80 በመቶ ከፍ ማለቱን በመጥቀስ የጉዳዩን አጣዳፊነት አጉልተው አሳይተዋል።
እ.ኤ.አ በ2024 ብቻ 4.43 ሚሊየን የወባ በሽታዎች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን ይህም ከሀገሪቱ "ቀዳሚ የሕዝብ ጤና ጠንቆች" አንዱ አድርጎታል።
ዘመቻው የወባ በሽታን በመዋጋት ረገድ ትልቅ እርምጃ የሆነው የ R21/Matrix-M ክትባት በብሔራዊ የክትባት ማስፋፊያ መርሃ-ግብር ውስጥ መካተቱን አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ