በንግድ ጦርነቶችና ክልላዊ ክፍፍል ምክንያት የኢኮዋስ ዕደገት በ2025 ከ5.1% ወደ 5.0% ይቀንሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበንግድ ጦርነቶችና ክልላዊ ክፍፍል ምክንያት የኢኮዋስ ዕደገት በ2025 ከ5
በንግድ ጦርነቶችና ክልላዊ ክፍፍል ምክንያት የኢኮዋስ ዕደገት በ2025 ከ5 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.07.2025
ሰብስክራይብ

በንግድ ጦርነቶችና ክልላዊ ክፍፍል ምክንያት የኢኮዋስ ዕደገት በ2025 ከ5.1% ወደ 5.0% ይቀንሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለፀ

ትንበያው በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) የኢንቨስትመንትና ልማት ባንክ የ2025 የምዕራብ አፍሪካ የልማት ምልከታ ላይ ተዘርዝሯል።

በዕድገት ምልከታው የተጠቀሱ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዋና ዋና ተግዳሮቶች፡-

▪ የአሜሪካ ቀረጦች፣

▪ የቡርኪናፋሶ፣ የማሊ እና የኒጀር ከኢኮዋስ መውጣት ንግድ ላይ የፈጠረው መስተጓጎል፣

▪ የሳህል ጥምረት በኢኮዋስ ምርቶች ላይ የሚጥለው የወጪ ንግድ ታክስና ኢኮዋስ ሊወስድ በሚችለው አፀፋዊ እርምጃ የንግድ እንቅስቃሴ መቀነስ፣

▪ በአሜሪካ የሚኖሩ የኢኮዋስ አባል ሀገራት ዜጎች የግብር ጭማሪን ተከትሎ የሚልኩት የገንዘብ መጠን መቀነስ፣

▪ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ግሽበት እና የወለድ ምጣኔ።

ℹ ሦስቱ የሳህል ጥምረት ሀገራት በጥር ወር ከኢኮዋስ በይፋ ለቀው ወጥተዋል። ማኅበረሰቡ ውሳኔያቸውን እንዲያስቡበት ቢያሳስብም የጥምረቱ አባላት ከማኅበረሰቡ ለቀው የመውጣት ውሳኔያቸው የመጨረሻ እንደሆነ በተከታታይ አረጋግጠዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0