- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የአፍሪካን ዕጣፈንታ መገንባት፦ የህዝብ አገልግሎት — በሀገር በቀል ፈጠራ እና ትብብር

የአፍሪካን ዕጣፈንታ መገንባት፦ የህዝብ አገልግሎት — በሀገር በቀል ፈጠራ እና ትብብር
ሰብስክራይብ
ዛሬ በናይሮቢ በተካሄደው 'የስማርት ገቨርንመንት' ጉባኤ የአፍሪካ ዲጂታል ሉዓላዊነት በዋናነት ተነስቷል — የህዝብ አግልግሎትን በእምነት፣ ግልጽነት እና ለዜጋ ቅድሚ በሰጠ ፈጠራ መምራት የሚለው ሀሳብም በሰፊው ተዳስሷል።
ዘንድሮ በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 21 — ሰኔ 23 የተከበረው በ10ኛው የአፍሪካ የህዝብ አገልግሎት ቀን ከአዲስ አበባ እስከ ጆሃንስበርግ ድረስ የአፍሪካ ሀገራት በአገር ውስጥ ፈጠራ፣ ፍትሃዊነት እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር የህዝብ አገልግሎትን መቀየር ላይ ትኩረት የሰጡበት ሆኗል።
የዘርፉ መሪዎችም ደማቅ ራዕዮችን አጋርተዋል፡-
🗣 "አፍሪካ ብቁ የሆኑ፣ የበለጠ ችሎታ ያላቸው ልጆች እንዲኖራት እንፈልጋለን... የትምህርት ስርዓታችን የበለጠ ቴክኒካል መሆን አለበት።" ክሊፎርድ ማቶሬራ፣ ከዚምባብዌ
ማሜሎ ሞናንግ፣ ከደቡብ አፍሪካ ስለ ብሪክስ ጥምረት ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት፣
"ካነሳናቸው ነገሮች አንዱ ከእነዚህ [ከብሪክስ አባል] አገሮች ጋር በመተባበር የተፈጠሩት እድሎች የራሳችንን እድገት እንዴት መቅረጽ እንደምንችል እና እርስ በእርሳችን መማር እንድንችል የሚያበረታቱ ናቸው፣" ሲሉ ተናግረዋል።
ሮምዋርድ ዲዮኒዚ ከታንዛኒያ አክለውም፣

"ማዕድናት አሉን ነገር ግን አውሮፓ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው እስክትነግረን እንጠብቃለን... BRICS ለአፍሪካ ድምፆች ጥሩ መድረክ ነው።" ብለዋል፡፡

አፍሪካ በሰዎች ላይ ያተኮረ እና በራስ የተመሰረተ አስተዳደር እንዴት እየገነባች እንደሆነ የበለጠ ለመረዳት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ይህንን የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ይከታተሉ።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0