ከአሜሪካ ወደ ሶስተኛ ሀገር የተባረሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች እስዋቲኒ ደረሱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከአሜሪካ ወደ ሶስተኛ ሀገር የተባረሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች እስዋቲኒ ደረሱ
ከአሜሪካ ወደ ሶስተኛ ሀገር የተባረሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች እስዋቲኒ ደረሱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.07.2025
ሰብስክራይብ

ከአሜሪካ ወደ ሶስተኛ ሀገር የተባረሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች እስዋቲኒ ደረሱ

የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር ከአምስት ሀገራት፤ የቬትናም፣ ጃማይካ፣ ላኦስ፣ ኩባ እና የመን ዜግነት ያላቸውን ስደተኞች የጫነ በረራ እስዋቲኒ ማረፉን አረጋግጧል።

እርምጃው የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ስደተኞች ሊደርስባቸው በሚችለው ጉዳት ላይ ይግባኝ የማለት መብታቸውን ነፍጎ ወደ ሶስተኛ ሀገራት ማዛወሩን በድጋሚ እንዲጀመር መፍቀዱን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

ህፃናትን አስገድዶ መድፈር እና ግድያን ጨምሮ ከባድ ወንጀሎችን ፈፅመዋል የተባሉት እነዚህ ግለሰቦች፤ ሀገሮቻቸው ሊቀበሏቸው ፍቃደኛ እንዳልሆኑ የአሜሪክ ደህንነት ቢሮ አስታውቋል፡፡

አዲስ የወጣው የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለሥልጣን (አይስ) ማስታወሻ እንዲህ ያሉት ስደተኞች ከስድስት ሰዓት ባነሰ ግዜ ውስጥ በአስቸኳይ ከሀገር ሊባረሩ እንደሚችሉ ይገልጻል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0