“የአፍሪካ አገራት በራሳቸው ፖሊሲ ሊተዳደሩ ይገባል”

ሰብስክራይብ

“የአፍሪካ አገራት በራሳቸው ፖሊሲ ሊተዳደሩ ይገባል”

ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ወጣት ዲፕሎማቶች ባዘጋጀችው "የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ሥልጠና" ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እየተሳተፈ የሚገኘው አናኬካ ክዋኬንዳ ጆኤል የተናገረው ነው፡፡

"አፍሪካዊያን በአንድነት መቆም አለብን፤ በውጭ ፖሊሲዎች መገዛታችንን ማቆም አለብን፤ የራሳችን ፖሊሲ ሊኖረን ይገባል። አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ክልላችንን እና አህጉራችንን ወደፊት ለማራመድ መቆም አለብን" ሲል ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ዲፕሎማቱ ወጣቶች የፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ አሕጉሪቱን ወደፊት ለማራመድ ያለውን ብርቱ ጉልበት በአግባቡ ሊረዱ እንደሚገባም አሳስቧል።

"እጅ ለእጅ ተያይዘን ከቆምን የተሻለች አፍሪካ ይኖረናል። ለመሪዎቻችን እና ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ የምፈልገው፤ ከሀገራችን ባሻገር ስለአህጉራችን ማሰብ ይገባናል። አንድ አይነት ሐሳብ፣ አንድ አይነት አላማ ካለን የተሻለች አፍሪካ ይኖረናል" ብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0