ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 100 ሚሊየን ሄክታር የደን ልማት ግብ ውስጥ 22 በመቶውን እስከ 2030 ድረስ ታሳካለች ተባለ
15:00 16.07.2025 (የተሻሻለ: 15:04 16.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከአፍሪካ 100 ሚሊየን ሄክታር የደን ልማት ግብ ውስጥ 22 በመቶውን እስከ 2030 ድረስ ታሳካለች ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 100 ሚሊየን ሄክታር የደን ልማት ግብ ውስጥ 22 በመቶውን እስከ 2030 ድረስ ታሳካለች ተባለ
ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ናቸው። የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ሀገራዊ ጥረት ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ እንደሆነ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
የደን ልማት የአፈር ጥበቃን፣ የውሃ ሃብት ልማትን፣ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትን፣ የግብርና ምርታማነትን እና የቱሪዝም እድገትን እንደሚደግፍ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን አሁን ላይ 23.6 በመቶ መድረሱንም አስታውሰዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ለግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት አነስተኛ አስተዋጽኦ ብታደርግም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X