አፋር ክልል ከውጭ ጎብኚዎች 8.6 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
13:38 16.07.2025 (የተሻሻለ: 13:44 16.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፋር ክልል ከውጭ ጎብኚዎች 8.6 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት 4 ሺህ 300 የውጪ ቱሪስቶች እንዲሁም ከ400 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ዜጎች በክልሉ የሚገኙ መስህቦችን እንደጎበኙ ገልጿል።
በክልሉ የሚገኙ ዋና የቱሪስት መዳረሻዎች ዳሎል፣ ኤርታሌ፣ አፍዴራ ሐይቅ፣ አላሎ ባድ ፈል፣ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፣ የአብዬ ሐይቅና ሌሎችን በማልማት ውጤት መገኘቱንም ጨምሮ ገልጿል።
ቢሮው በአፋር ክልል የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት የዘርፉን እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየሠራ እንደሆነ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግሯል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X