ኢትዮጵያ ለወጣት ምስራቅ አፍሪካዊያን ዲፕሎማቶች የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ሥልጠና መስጠት ጀመረች
17:49 15.07.2025 (የተሻሻለ: 18:14 15.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ለወጣት ምስራቅ አፍሪካዊያን ዲፕሎማቶች የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ሥልጠና መስጠት ጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለወጣት ምስራቅ አፍሪካዊያን ዲፕሎማቶች የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ሥልጠና መስጠት ጀመረች
የወጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው ሥልጠና ከሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ የተውጣጡ አዳዲስ ዲፕሎማቶችን አሰባስቧል፡፡
የሥልጠናው ዓላማዎች፦
🟠 የጋራ መግባባትን ማዳበር፣
🟠 ዲፕሎማሲያዊ ክህሎቶችን ማሻሻል፣
🟠 ቀጣናዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮችን በጋራ መወጣት፣
🟠 በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር፣
🟠 ዲፕሎማቶች በዓለም አቀፍ መድረክ የጋራ ቀጣናዊ ጥቅሞችን ማስከበር እንዲችሉ መደገፍ፡፡
የውጭ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አዳም ተስፋዬ "ቀጣናችን አንድ ሀገር ብቻውን ሊወጣቸው የማይችላቸው መለከ ብዙ ፈተናዎች ያጋጥሙታል" ያሉ ሲሆን፤ "ይህ ፕሮግራም የጋራ ግባችንን ለማሳካት የጋራ ጥበብን እና የጋራ ቁርጠኝነትን ለመጠቀም ወሳኝ እርምጃ ነው" ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ሥልጠናው ትናንት የጀመረ ሲሆን እስከ ሐምሌ 11 ድረስ ይቆያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
