ብሔራዊ የንፁህ ምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታ ለ335 ሺህ የሥራ እድል ይፈጠራል ተባለ
17:33 15.07.2025 (የተሻሻለ: 17:34 15.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብሔራዊ የንፁህ ምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታ ለ335 ሺህ የሥራ እድል ይፈጠራል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ብሔራዊ የንፁህ ምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታ ለ335 ሺህ የሥራ እድል ይፈጠራል ተባለ
3.8 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ የሚደረግበት ሀገራዊ እቅድ 2 ሚሊየን ሴቶችንም ያበቃል ሲል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በቀጣዮቹ 10 ዓመት ውስጥ የሚተገበረው ብሔራዊ እቅድ ከባሕላዊ ምግብ ማብሰያ (የእንጨትና ኩበት) ወደ ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ መፍትሄዎች ለማሸጋገር አልሟል፡፡
በተጨማሪም ፍኖተ ካርታው፦
🟠 በ2035 የንፁህ ምግብ ዝግጅት ተደራሽነትን ከ9 በመቶ ወደ 75 በመቶ ቤተሰቦች ለማሳደግ፣
🟠 በአጠቃላይ 36 ሚሊየን ዘመናዊ ምድጃዎችን በመላ ሀገሪቱ ማሰራጨት፣
🟠 የከተማና የገጠር ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ፣ የፀሐይና የማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዷል።
መንግሥት ከጠቅላላ ወጪው 10% ማለትም 380 ሚሊዮን ዶላር ይሸፍናል። ቀሪው ከግል ዘርፍ እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ይጠበቃል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X