ሰርጌ ላቭሮቭ ከሻንጋይ የትብብር ድርጀት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኋላ የሰጡት ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰብስክራይብ

ሰርጌ ላቭሮቭ ከሻንጋይ የትብብር ድርጀት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኋላ የሰጡት ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ

ዋና ዋና መግለጫዎች፦

ሩሲያን በተመለከተ ትራምፕ ሰለሰጡት መግለጫ፦

▪ ሩሲያ ትራምፕ ዩክሬንን ግጭት በ50 ቀናት ውስጥ እልባት እንዲያገኝ ከጠየቁበት መግለጫቸው በስተጀርባ ያለውን አቋም መገንዘብ ትፈልጋለች፡፡

▪ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኪዬቭ በጦር መሣሪያ እንድትሞላ በሚጠይቀው የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው ነው፡፡

▪ ሩሲያ አዲስ ማዕቀቦች ቢጣሉባት እንኳ የመወጣት አቅም አላት፡፡

▪ የሩሲያ የንግድ አጋሮች ግዴታቸውን ሊተዉ አይችሉም፡፡

▪ አውሮፓ ሕብረት አሜሪካን ወደ "አዲስ ፀረ-ሩሲያ ማዕቀብ አዙሪት" ለማስገባት እየሞከረ ነው፤ ነገር ግን የሚጎዱት እነዚሁ የማዕቀብ ጦርነት ደጋሾች ናቸው፡፡

የዩክሬን ግጭት እልባትን በተመለከተ፡-

▪ ሩሲያ የኢስታንቡል የውይይት መድረክ እንዳላበቃለት ታምናለች፤ አሜሪካም ስለዚህ አቋም ታውቃለች፡፡

▪ የኢስታንቡል የውይይት መድረክ እንዳበቃለት የሚገልጹት የኪዬቭ መግለጫዎች ለሰላም ፍላጎት እንደሌላት ማሳያዎች ናቸው፡፡

▪ በኢስታንቡል ድርድሮች ምንም መሻሻል አልነበረም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡

ኢራንን በተመለከተ፦

▪ የሻንጋይ የትብብር ድርጀት አባል ሀገራት ቴሕራን የኒውክሌር ኃይልን ለሰላም አገልግሎት የመጠቀም መብት እንዳላት አረጋግጠዋል፡፡

▪ የቴሕራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቀውስ በእውነተኛ እና በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች በላቭሮቭ እና በኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ስብሰባ ወቅት ውይይት ተድርጎበታል፡፡

▪ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔው ቴሕራን ከረጅም ጊዜ በፊት የገለጸቻቸውን ውሳኔዎች ማለትም የኒውክሌር ጦር መሣሪያን በይፋ ማቆሟን ማክበር ይኖርበታል፡፡

▪ የእልባቱ በጣም አስፈላጊው መርህ ኢራን ዩራኒየምን ለኃይል ዓላማ የማበልጸግ ሕጋዊ መብቶቿን ማክበር ነው፡፡

▪ ኢራን በእስራኤል እና በአሜሪካ ጥቃቶች የወደሙ መሠረተ ልማቶቿን ለመጠገን የሩሲያን እርዳታ አልጠየቀችም፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0