ኢትዮጵያ ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር በመተባባር ምስራቅ አፍሪካን በኒውክሌር ምርምር ማስተሳሰር ትችላለች - የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር በመተባባር ምስራቅ አፍሪካን በኒውክሌር ምርምር ማስተሳሰር ትችላለች - የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው
ኢትዮጵያ ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር በመተባባር ምስራቅ አፍሪካን በኒውክሌር ምርምር ማስተሳሰር ትችላለች - የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር በመተባባር ምስራቅ አፍሪካን በኒውክሌር ምርምር ማስተሳሰር ትችላለች - የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ ”በጎርጎሮሳውያኑ 2019 የመገባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የሩሲያ አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን (ሮሳቶም)፣ በርካታ የሙያ ዘርፎችን ጨምሮ የኢትዮጵያን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመደገፍ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ ነው” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን አጋርነት ለማሳካት በርካታ ስትራቴጂያዊ እርምጃዎችን መውሰድ ትችላለች የሚሉት ቸሬ፤ ቀጣናዊ ሥልጠናን እና የእውቀት ሽግግር ማበረታታትን ለአብነት ጠቀሰዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ከሮሳቶም ጋር በመደራደር ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ ከምስራቅ አፍሪካ ጎረቤት ሀገራት ለሚመጡ ባለሙያዎች እና ተማሪዎችም ክፍት የሚሆን፣ የኒውክሌር ማሠልጠኛ ማዕከል ወይም የነፃ ትምህርት ዕድል ፕሮግራም ማቋቋም ትችላለች፡፡”

ተመራማሪው በቀጣናው የአቅም ግንባታን ማጎልበት በጣም ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤ በሌላ በኩል የጋራ ምርምር እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ያስፈልጋሉ ይላሉ፡፡

"ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ በሮሳቶም የሚደገፍ፤ በምስራቅ አፍሪካ እንደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ሱዳን ያሉ በርካታ ሀገራትን የሚያገለግል የማምረቻ መሠረተ ልማት ወይም የኒውክሌር ምርምር ማብለያ የራዲዮቴራፒ ማዕከል እንዲቋቋም በማድረግ የጋራ ቀጣናዊ ፕሮጀክቶችን ለማልማት ግፊት ማድረግ ትችላለች" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0