የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃ መንዛታቸውን ቀጥለዋል
14:34 15.07.2025 (የተሻሻለ: 15:54 15.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃ መንዛታቸውን ቀጥለዋል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃ መንዛታቸውን ቀጥለዋል
ትናንት በኋይት ሃውስ ከኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩተ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ በሰጡት ገለፃ፤ "ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወደ ናይል የሚሄደውን ውኃ የሚዘጋ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ "በአጋጣሚ ግድቡን ሠርተዋል (ኢትዮጵያውያን)፤ ይህም ወደ ናይል የሚሄደውን ውኃ የሚዘጋ ነው። እንደማስበው እኔ ግብፅን ብሆን ውኃው ወደ ናይል እንዲፈስ እፈልጋለሁ። እናም በዚህ ነገር ላይ እየሠራን ነው። ይህም ችግር መፍትሄ በሚያገኝበት አግባብ ላይ ነው" ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከ3 ሳምንት በፊት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "በጅልነት በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ነው" ሲሉ የሰጡትን ሐሳብም፤ "ዩናይትድ ስቴትስ ለግድቡ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገች ይመስለኛል" ሲሉ በድጋሚ አንጸባርቀውታል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አረጋዊ በርሔ ትራምፕ ግድቡን አስመልክቶ የሰነዘሩትን አስተያየት ውድቅ ባደረጉበት ምላሻቸው፤ "ሕዳሴ ግድብ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት፣ ጉልበት፣ እውቀትና በኢትዮጵያ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እየተገነባ ያለ ነው” ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/