በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኦሞ ወንዝ ሙላት ባስከተለው ጎርፍ 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ
13:07 15.07.2025 (የተሻሻለ: 13:14 15.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኦሞ ወንዝ ሙላት ባስከተለው ጎርፍ 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ
በክልሉ ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች በኦሞ ወንዝ ሙላት ሙሉ በሙሉ እንደተጥለቀለቁ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በኦሞ ወንዝ ሙላት የወረዳው ዋና ከተማ የሆነችው ኦሞራቴ ከተማ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በውሃው የመዋጥ ስጋት ውስጥ መግባቷም ነው በዘገባው የተመላከተው።
የኦሞ ወንዝ ሞልቶ የቱርካና ሐይቅ ከኦሞራቴ ከተማ ከዚህ ቀደም ከነበረው 60 ኪ.ሜ ርቀት አልፎ አሁን ላይ ወደ 1.3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መጠጋቱ ምንጮቹ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X