የሩሲያው ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ጀምሮ በናኖባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያስተምር ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያው ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ጀምሮ በናኖባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያስተምር ነው
የሩሲያው ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ጀምሮ በናኖባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያስተምር ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.07.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያው ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ጀምሮ በናኖባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያስተምር ነው

“ከኢትዮጵያ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን፣ በሚቀጥለው ዓመት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የባዮፊዚክስ ማስተርስ መርሃ ግብር ምዝገባ ለመጀመር እያቀድን ነው፡፡ ትምህርታቸውንም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀምርሉ” ሲሉ በዩኒቨርስቲው የከፍተኛ ጥናቶች ተቋም ዳይሬክተር ማክሲም ዬቭስቲግኔዬቭ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ትብብሩ ሴቭኤስዩ እና አዳማ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የጋራ የምርምር እንቅስቃሴዎችን መጀመራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ በተጨማሪም ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሚጋበዙ ፕሮፌሰር የሩሲያውን ዩኒቨርስቲ የሳይንስ ቡድን ከፈረንጆቹ 2026 በኋላ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

“በሴቭኤስዩ ወጣት ሳይንቲስቶችን አስተምረው ወደ ምርምር ቡድናቸው መመለሳቸው የአዳማ ዩኒቨርሲቲን የምርምር ጥራት ለማሻሻል እንደሚረዳቸው ያምናሉ፡፡ በሴቫስቶፖል በሚቆዩበት ጊዜ በምርምር ቡድኖቻችን ውስጥ ስለሚካተቱ ልምድ መጋራት ይችላሉ” ሲሉ የተቋሙ ዳይሬክተር አስረድተዋል።

ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ (ሴቭኤስዩ) ክራይሚያ እና ሴቫስቶፖል ወደ ሩሲያ ዳግም ከተዋሃዱ በኋላ የተቋቋመ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሴቫስቶፖል ትልቁ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን በክራይሚያ ባሕረ ሰላጤ ከሚገኙ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥም አንዱ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0