አውሮፓ በጎርጎሮሳውያኑ 2030 ከፍተኛ ጦርነት ሊገጥማት ይችላል ሲል የፈረንሳይ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተነበየ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአውሮፓ በጎርጎሮሳውያኑ 2030 ከፍተኛ ጦርነት ሊገጥማት ይችላል ሲል የፈረንሳይ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተነበየ
አውሮፓ በጎርጎሮሳውያኑ 2030 ከፍተኛ ጦርነት ሊገጥማት ይችላል ሲል የፈረንሳይ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተነበየ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.07.2025
ሰብስክራይብ

አውሮፓ በጎርጎሮሳውያኑ 2030 ከፍተኛ ጦርነት ሊገጥማት ይችላል ሲል የፈረንሳይ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተነበየ

የፈረንሳይ የመከላከያና የብሔራዊ ደህንነት ጠቅላይ መምሪያ “አሁን ወደ አዲስ የዘመን ምዕራፍ እየገባን መሆኑ ግልጽ ነው፤ ይህም በአውሮፓ ኃያል ጦርነት የመከሰት አደጋ ያለበት ነው፡፡ በ2030 ከብሔራዊ ግዛታችን ውጭ፤ ፈረንሳይንና አጋሮቿን በተለይም አውሮፓውያንን የሚያሳትፍ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ግዛቶቻችን በልዩ ልዩ ጥቃቶች ዒላማ የሚሆኑበት ሁኔታ እናያለን” ሲል በ2025ቱ ብሔራዊ ስትራቴጂካዊ ግምገማ ላይ አስቀምጧል፡፡

ከሦስት እስከ አምስት ዓመት ውስጥ ሩሲያ በአውሮፓ ላይ ወረራ ልትፈጽም የምትችልበትንም እድል ሰነዱ ያትታል፡፡ ሞስኮ በሞልዶቫ፣ በባልካን ሀገራት ወይም በኔቶ ሀገራት ላይ ጭምር ጥቃት ልትጀምር ትችላለችም ብሏል ግምገማው፡፡

ሞስኮ ኔቶን ወይም የአውሮፓ ሀገራትን የማጥቃት እቅድ እንደሌላት ደጋግማ ተናግራለች። ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ኔቶን ለማጥቃት እየተዘጋጀች ነው የሚሉ ሰዎች እንኳን የሚናገሩትን አያምኑትም ብለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0