የሱዳን ጦር በማዕከላዊ ሱዳን ከፈጠኖ ደራሽ ኃይሉ ስትራቴጂያዊ አካባቢ መቆጣጠሩን የዳርፉር አስተዳዳሪ ተናገሩ
20:23 14.07.2025 (የተሻሻለ: 20:24 14.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሱዳን ጦር በማዕከላዊ ሱዳን ከፈጠኖ ደራሽ ኃይሉ ስትራቴጂያዊ አካባቢ መቆጣጠሩን የዳርፉር አስተዳዳሪ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሱዳን ጦር በማዕከላዊ ሱዳን ከፈጠኖ ደራሽ ኃይሉ ስትራቴጂያዊ አካባቢ መቆጣጠሩን የዳርፉር አስተዳዳሪ ተናገሩ
የዳርፉር ክልላዊ ገዥ ሚኒ ሚናዊ፤ በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት የሚገኘው ኡም ሱመያ አካባቢ ነፃ መውጣቱን አስታውቀዋል፡፡
አካባቢው ከክልሉ ዋና ከተማ ኤል ኦቤይድ በስተምዕራብ የሚገኝ ሲሆን ካርቱም ወይም ኤል ፋሸርን ከመሳሰሉ ዋና ዋና ከተሞች ጋር የተገናኘና የአየር ማረፊያም ያለው ነው፡፡ የሱዳን ጦር ከተማውን ከሞላ ጎደል ለአንድ ዓመት ከብቦ ይዞ የቆየውን የሱዳን ፈጠኖ ደራሽ ኃይል ሰብሮ ገብቷል፡፡
ኤል ኦቤይድ በቅርቡ በሱዳን ፈጠኖ ደራሽ ኃይል አማፅያን ከፍተኛ ጥቃት አስተናግዷል። ባለፈው ሳምንት ታጣቂዎቹ በከተማው ላይ መድፍ በመተኮስ ንጹሃን ዜጎችን ዒላማ እንዳደረጉ የሱዳን ዶክተሮች ኔትወርክ ገልጿል፡፡
የህክምና ድርጅቱ "የኤል ኦቤይድ አጎራባች አካባቢዎች በፈጠኖ ደራሽ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ካሉ አካባቢዎች በተፈናቀሉ እና በሸሹ ሰዎች ተጨናንቀዋል" ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጃ መሠረት፤ ከጎርጎሮሳውያኑ ሃምሌ 6 እስከ 12 ባለው ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት በተወሰኑ አካባቢዎች ወደ 1 ሺህ 400 የሚጠጉ አባወራዎች ተፈናቅለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X