ትራምፕ ከኔቶ አለቃ ማርክ ሩተ ጋር ከነበራቸው ስብሰባ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
19:06 14.07.2025 (የተሻሻለ: 19:14 14.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ ከኔቶ አለቃ ማርክ ሩተ ጋር ከነበራቸው ስብሰባ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
▪ በ50 ቀናት ውስጥ ከዩክሬን ጋር ስምምነት ካልተደረሰ አሜሪካ በሩሲያ እና በንግድ አጋሮቿ ላይ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ ትጥላለች፡፡
▪ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ሞስኮ እና ዋሽንግተን ከስምምነት ላይ ካልደረሱ፤ አሜሪካ በሩሲያ እና በንግድ አጋሮቿ ላይ 100% የገቢ ቀረጥ ትተገብራለች፡፡
▪ አሜሪካና እና ኔቶ በአውሮፓ ወጪ የጦር መሣሪያዎችን ለዩክሬን ለማቅረብ ተስማምተዋል፡፡
▪ አዲሱ የአሜሪካ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ሥርዓቶችን የሚያካትትና መሰል 17 ሥርዓቶችን ማቅረብ ከግምት ውስጥ ግብቷል፡፡
▪ አሜሪካ ለዩክሬን የምታቀርባቸው ጦር መሣሪያዎች ቅንጅት በኔቶ እና በጥምረቱ የአሜሪካ አምባሳደር ዊትከር በኩል ይሳለጣል፡፡
▪ ሁለቱም ማለትም ሩሲያ እና ዩክሬን የመፍትሄ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ እና የአሜሪካ አዲስ ማዕቀቦች እንደማያስፈልጉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት እርግጠኛ ናቸው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X