በ2025 በአፍሪካ ከ26 ሺ በላይ ሰዎች በኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) የተያዙ ሲሆን፤ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሽታው ፀንቶባታል
17:43 14.07.2025 (የተሻሻለ: 17:44 14.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበ2025 በአፍሪካ ከ26 ሺ በላይ ሰዎች በኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) የተያዙ ሲሆን፤ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሽታው ፀንቶባታል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በ2025 በአፍሪካ ከ26 ሺ በላይ ሰዎች በኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) የተያዙ ሲሆን፤ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሽታው ፀንቶባታል
ከጎርጎሮሳውያኑ ጥር ጀምሮ፣ በ21 የአፍሪካ ሀገራት 26 ሺህ 734 ሰዎች በኤምፖክስ እንደተያዙ ተመዝግቧል፡፡ 115 ሰዎች መሞታችውንም በመንግሥታቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (ኦቻ) በኩል የወጣው የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 13 ሺህ 545 በበሽታው የተያዙ ሰዎችንና 38 ሞት በመመዝገብ ከፍተኛውን የጉዳት ድርሻ ይዛለች፡፡ ኡጋንዳ 6 ሺህ 51፤ ሲራሊዮን ደግሞ 4 ሺህ 610 ሰዎችን በመመዝገብ ይከተላሉ፡፡
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኮንጎ እና በሴራሊዮን የበሽታው ስርጭት ምጣኔ እየቀነሰ ቢመጣም፤ ይህ በምርመራ መዘግየት እና በምላሽ አቅም ማነስ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቀቋል፡፡
ℹ በአውሮፓውያኑ ግንቦት 2023 የተነሳው የኤምፖክስ (ዝንጀሮ ፈንጣጣ) የዓለም ጤና ስጋትነት፤ በነሃሴ 2024 ቫይረሱ በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ ዳግም አግረሽቶ እንደገና ወደነበረበት ተመልሷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X