የቻይና የኪነጥበብ ቡድን የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክር የጥበብ ሥራዎችን በኢትዮጵያ አቀረበ
16:22 14.07.2025 (የተሻሻለ: 16:34 14.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቻይና የኪነጥበብ ቡድን የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክር የጥበብ ሥራዎችን በኢትዮጵያ አቀረበ
በምስራቅ ጋኦ ያን ሞንጎሊያ አርት ቲያትር ምክትል ፕሬዝዳንት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የቻይና የኪነጥበብ ቡድን ሥራዎቹን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት አዳራሽ አቅርቧል።
ፕሮግራሙ የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 55ኛ ዓመትን አስመልክቶ የተካሄደ እንደሆነ ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዝግጅቱ ሁለቱ ሀገራት በኪነጥበቡ እና በባህሉ ዘርፍ የልምድ ልውውጥ ያካሄዱበት እንደነበርም ተጠቁሟል። በቀጣይ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ቡድን ወደ ቻይና በማቅናት የኢትዮጵያን ባሕልና እሴቶች እንደሚያስተዋውቅ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X