ትራምፕ የረዥም ርቀት ጃስም ሚሳኤሎችን ለኪዬቭ ለማቅረብ እያጤኑ ነው ሲል ሚሊታሪ ዎች መጽሔት ዘገበ
15:51 14.07.2025 (የተሻሻለ: 15:54 14.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ የረዥም ርቀት ጃስም ሚሳኤሎችን ለኪዬቭ ለማቅረብ እያጤኑ ነው ሲል ሚሊታሪ ዎች መጽሔት ዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ የረዥም ርቀት ጃስም ሚሳኤሎችን ለኪዬቭ ለማቅረብ እያጤኑ ነው ሲል ሚሊታሪ ዎች መጽሔት ዘገበ
የሚሳኤሉ የመጀመሪያ ስሪት 370 ኪ.ሜ ርቀት መወንጨፍ ይችላል። ማሻሻያ የተደረገለት ጃስም-ኢአር በበኩሉ 1 ሺህ ኪ.ሜ ርቀት ድረስ ይተኮሳል።
ሩሲያ ለኪዬቭ የሚደረግ የምዕራባውያን ሀገራት የጦር መሣሪያ አቅርቦትን በጽኑ ትቃወማለች። ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ፣ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛካሮቫ እና የክሬሚልን ቃል አቀባይ ፔስኮቭ፤ መሰል አቅርቦት በዩክሬን ግጭት ውስጥ የጦር መሣሪያ አቅራቢዎችን በቀጥታ የሚያሳትፍ፣ የሰላም ውይይቱን የሚገታ እና የግጭቱን ጊዜ የሚያራዝም መሆኑን በተደጋጋሚ ተናረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን፣ መሣሪያዎቹ ያለአምራች ሀገራት ወታደራዊ ባለሙያዎች እገዛ እንዳለመሥራታቸው በምዕራባውያን የረዥም ርቀት መሣሪያዎች ሩሲያን ላይ የሚደርስ የዩክሬናውያኑ ጥቃት ኔቶን በግጭቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X