የሞስኮ እና ኪዬቭ ድርድር እንደሚቀጥል የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለመገናኛ ብዙኃን ተናገሩ
14:45 14.07.2025 (የተሻሻለ: 14:54 14.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሞስኮ እና ኪዬቭ ድርድር እንደሚቀጥል የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለመገናኛ ብዙኃን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሞስኮ እና ኪዬቭ ድርድር እንደሚቀጥል የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለመገናኛ ብዙኃን ተናገሩ
ሩሲያ እና ዩክሬን ሁለት ዙር ቀጥተኛ ድርድር ኢስታንቡል ውስጥ አካሂደዋል። ድርድሩ የእስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ አስችሏል። በተጨማሪም ሩሲያ የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለኪዬቭ አስረክባለች።
በተጨማሪም ተደራዳሪ ወገኖች በግጭቱ እልባት ላይ ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ ተለዋውጠዋል። የቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ምንጭ ቀደም ሲል ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ አንካራ በኢስታንቡል ሶስተኛው ዙር ድርድር የሚካሄድበትን ቀን በተመለከተ ከሩሲያ እና ዩክሬን ውሳኔ እየጠበቀች ነው።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ሶስተኛ ዙር ድርድር ለማካሄድ ዝግጁ መሆኗን ከዚህ ቀደም ደጋግማ ገልፃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X