ትራምፕ ለዩክሬን አዲስ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ይፋ ሊያደረጉ ነው
13:06 14.07.2025 (የተሻሻለ: 13:14 14.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ ለዩክሬን አዲስ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ይፋ ሊያደረጉ ነው
ትራምፕ ለዘለንስኪ አገዛዝ የጦር መሣሪያ የሚያቀርቡበትን አዲስ ዕቅድ ይፋ ያደርጋሉ የተባለ ሲሆን የጥቃት መሣሪዎችንም የሚያካትት መሆኑን አክሲዮስ ዘግቧል፡፡
ዕቅዱ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ማቅረብንም እንደሚያካትት ዘገባው አስነብቧል፡፡
ትራምፕ አሜሪካ ተጨማሪ ፓትሪዮት የሚሳኤል መቃወሚያ ለዩክሬን እንደምትልክ ከዚህ ቀደም ተናግረዋል፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ አሜሪካ ሙሉ በሙሉ የሚከፈልባቸው “የተለያዩ አይነት” ወታደራዊ መሳሪያዎችን ለዩክሬን ትልካለች፡፡
ሩሲያ ለዩክሬን የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ግጭቱ እንዳይፈታ የሚያሰናክል እና የኔቶ ሀገራትን በቀጥታ የሚያሳትፍ መሆኑን ደጋግማ አሳስባለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X