የኢራን ፕሬዝዳንት በእስራኤል ጥቃት መቁሰላቸው ተሠማ
19:51 13.07.2025 (የተሻሻለ: 19:54 13.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢራን ፕሬዝዳንት በእስራኤል ጥቃት መቁሰላቸው ተሠማ
ማሱድ ፔዜሽኪያን እስራኤል ሰኔ 16 ቀን ቴሕራን ውስጥ ባካሄደችው ጥቃት ቀላል የእግር ጉዳት እንደደረሠባቸው እንድ የኢራን ሚዲያ ዘገቧል። ጉዳቱ በእስራኤል ከተመታ ሕንፃ ለቀው በሚወጡበት ወቅት ነው የደረሠባቸው።
ጥቃቱ በምዕራብ ቴሕራን የሉዓላዊ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት የተሰበሰበበትን ህንፃ ኢላማው ያደረገ ነበር።
በርካታ ባለሥልጣናትም ከጥቃቱ ሲያመልጡ መጠነኛ የእግር ጉዳት ማስተናገዳቸውን የዜናው ምንጭ ገልጿል፡፡
የመውጫ መንገዶችን እና የአየር ፍሰትን ለመዝጋት በሕንፃው መግቢያ እና መውጫዎች ላይ ስድስት ተተኳሽ ሚሳኤሎች እንደተተኮሱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ከፍንዳታው በኋላ መብራት እንደጠፋና ተሰበሳቢዎቹ አስቀድሞ በተሰናዳላቸው የአደጋ ጊዜ መውጫ በኩል መውጣት ችለዋል ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X