ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሩሲያ ኩባንያዎች የአልማዝ ማዕድን እንዲያወጡ ፈቀደች
19:05 13.07.2025 (የተሻሻለ: 19:14 13.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሩሲያ ኩባንያዎች የአልማዝ ማዕድን እንዲያወጡ ፈቀደች
ባለፈው ዓመት በ ’ኪምበርሊ ሂደት’ የአልማዝ የወጪ ንግድ እገዳ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው፤ የሀገሪቱ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቴሪ ፓትሪክ አኮሎዛ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
"ምክንያቱም ያለ ማዕቀብ ሀገሪቱ የማልማትና የማዕድን ምርቶቿን በመሸጥ ጥሩ ገቢ የማግኘት እድል አላት” በማለት አዲሱ ነጻነት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ አቅም አጉልተው አሳይተዋል፡፡
በጎረጎሮሳውያኑ ሕዳር 21፣2024 ለአልማዝ ንግድ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚሰጠውና ተቆጣጣሪ አካል የሆነው ‘የኪምበርሊ ሂደት’ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አልማዝ ወደ ውጭ እንዳትልክ ጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል፡፡ እቀባው በግጭት ስጋት ምክንያት መጀመሪያ የተጣለባት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፡፡
በ2016 እግዱ በከፊል መነሳቱን ተከትሎ ከግጭት ነጻ ከተባሉ አምስት ቀጠናዎች አልማዝ ወደ ውጭ እንድትልክ አስችሏታል፡፡ የማዕቀቡ ሙሉ በሙሉ መነሳት ደግሞ ለሰፊ የማዕድን ሥራዎች እና ለዓለም አቀፍ አጋርነት መንገድ ከፍቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X