የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ

አየር መንገዱ ከዓለም ግንባር ቀደም እና ተወዳዳሪ የአቪዬሽን ኩባንያዎች መካከል ለመሆን የወጠነውን 2030 ራዕይ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ አቪየሽን መሪው ከቦይንግ እና ኤርባስ 120 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙንም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ አስታውቀዋል።

“የኤርባስ350 አውሮፕላን ለመግዛት አዘናል። በአሁኑ ሰዓት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን እየተረከብን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

🟠 በሽሬ፣

🟠 ነቀምት እና

🟠 ደምቢዶሎ ከተሞች አዳዲስ ተርሚናሎች ለመገንባት እቅድ መያዙንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የኮምቦልቻ ተርሚናል በሐምሌ ወር መጨረሻ እንዲሁም የያቤሎ ኤርፖርት በነሐሴ ወር እንደሚመረቅ ገልፀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0