ኡጋንዳ ከ900 ሺህ በላይ አባወራዎችን በነጻ ኃይል ልታገናኝ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኡጋንዳ ከ900 ሺህ በላይ አባወራዎችን በነጻ ኃይል ልታገናኝ ነው
ኡጋንዳ ከ900 ሺህ በላይ አባወራዎችን በነጻ ኃይል ልታገናኝ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2025
ሰብስክራይብ

ኡጋንዳ ከ900 ሺህ በላይ አባወራዎችን በነጻ ኃይል ልታገናኝ ነው

በኤሌክትሪክ ተደራሽነት ማሳደጊያ ፕሮጀክት የኡጋንዳ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ኩባንያ እና የኢነርጂ ሚኒስቴር የውጤት ተኮር የገንዘብ ድጎማ እና የቁሳቁስ አቅርቦት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጎማ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ማሳደጊያ ፕሮጀክት ኩባንያው ለመነሻ 508 ሺህ 35 አዲስ የኃይል ማከፋፈያዎች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ሚኒስቴሩ ደግሞ እያንዳንዱን ማከፋፈያ በገለልተኛ አካል ካረጋገጠ በኋላ የኩባንያውን ወጪ ይከፍላል፡፡

የቁሳቁስ አቅርቦት ስምምነቱ 388 ሺህ 400 አዳዲስ የኃይል ግንኙነቶችን መፍጠር ይሸፍናል። ሚኒስቴሩ በአንጻሩ እንደ ምሰሶዎች፣ ኮንዳክተሮች እና ሜትሮች ያሉ ቁሳቁሶችን ያቀርባል፡፡

ሁለቱ ስምምነቶች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ከ60 በመቶ ወደ 100 በመቶ ለማሳደግ የወጠነውን የኡጋንዳ ኢነርጂ ፖሊሲ እና የሽግግር እቅድ ይደግፋል።

ፕሮጀክቱ 500 ሜጋ ዋት የኃይል ፍላጎት በማቀረብ የሚከተሉትን ዒላማ አድርጓል፦

🟠 ትምህርት ቤቶች፣

🟠 ጤና ጣቢያዎች፣

🟠 ኢንዱስትሪ ፓርኮች፣

🟠 የንግድ ሥራዎች ናቸው።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0