ናይጄሪያ ባስቀጠለችው የፀረ ሽብር ችሎት ቦኮ ሃራምን በገንዝብ የሚደግፉ 44 ሰዎችን በእስር ቀጣች
15:55 13.07.2025 (የተሻሻለ: 16:04 13.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ ባስቀጠለችው የፀረ ሽብር ችሎት ቦኮ ሃራምን በገንዝብ የሚደግፉ 44 ሰዎችን በእስር ቀጣች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ ባስቀጠለችው የፀረ ሽብር ችሎት ቦኮ ሃራምን በገንዝብ የሚደግፉ 44 ሰዎችን በእስር ቀጣች
ይህም ከሰባት ዓመት በፊት ተቋረጦ የነበረው የተጠርጣሪ ታጣቂዎች ክስ ዳግም መጀመሩን የሚያመላክት መሆኑን የሀገሪቱ የፀረ ሽብር ማዕከል ቃል አቀባይ አቡ ማይክል ቅዳሜ አስታውቀዋል፡፡
"ችሎቱ የጉልበት ሥራ የሚጨምር ከ10 እስከ 30 ዓመት የሚደርስ እስራት ብይን ሰጥቷል” ሲሉ ማይክል ተናግረዋል፡፡ "ናይጄሪያ አሁን ላይ የቅርብ ጊዜ የጥፋተኝነት ብይኖች ጨምሮ በድምሩ 785 ሽብርን በገንዘብ መደገፍ እና ሌሎች ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን ይዛለች፡፡"
በኒጀር ግዛት ካይንጂ ወታደራዊ ካምፕ ከተቋቋሙ አራት ልዩ ሲቪል ፍርድ ቤቶች የ54 ተጠርጣሪዎች የቅጣት ብይን ተስጠቷል፡፡ የቀሪ 10 ተጠርጣሪዎች ችሎት ለሌላ ቀን ተላልፏል።
ናይጄሪያ ቀደም ብሎ ከጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት 2017 ጀምሮ እስላማዊ አማፂዎች ላይ መዘገብ ከፍታ የጅምላ ክስ አካሂዳለች፡፡ አምስት ወር በፈጀ ምዕራፍ በ200 የጀሃዲስት ተዋጊዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X