ኢትዮጵያዊው የመካኒካል ኢንጂነር ባሕላዊ እርሻን ያዘምናል የተባለለት የጓሮ አትክልት ዘር መትከያ ፈጠረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያዊው የመካኒካል ኢንጂነር ባሕላዊ እርሻን ያዘምናል የተባለለት የጓሮ አትክልት ዘር መትከያ ፈጠረ
ኢትዮጵያዊው የመካኒካል ኢንጂነር ባሕላዊ እርሻን ያዘምናል የተባለለት የጓሮ አትክልት ዘር መትከያ ፈጠረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያዊው የመካኒካል ኢንጂነር ባሕላዊ እርሻን ያዘምናል የተባለለት የጓሮ አትክልት ዘር መትከያ ፈጠረ

መካኒካል መሃንዲስ፣ የማኑፋክቸሪንግ አሠልጣኝ እና በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህር የሆነው ፍሰሃ ስንታየሁ ገጠራማ አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮችን ሥራ የሚያቀልል እና ምርታማነትን የሚጨምር ዘር መትከያ ማሽን ፈጥሯል፡፡

 

‍ የገጠር አርሶ አደሮችን የሥራ ጫና በእጅጉ በማቃለል እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ድንች እና ቀይ ሽንኩርት ያሉ የጓሮ አትክልቶችን ለመትከል የተነደፈ አብዮታዊ ማሽን መሆኑን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጿል፡፡

እንደ ፍሰሃ ማብራሪያ፦

ማሽኑ በአንድ ሰው የሚንቀሳቀስ ነው፣

ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በተገቢው ጥልቀት ዘር መትከል ይችላል፣

ዘር መዝራት እና ማዳበሪያ መርጨትን አዋህዷል።

"ይህ ማሽን በዘልማዳዊ የመትከል ሂደት ያለውን አሰልቺ የጉልበት ሥራ የሚያስቀር እና በማኅበረሰባችን ውስጥ የእርሻ ልምምድን የማሸጋገር አቅም አለው" ብሏል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0