ዚምባብዌ አደንዛዥ እፅ እና ሱስ ተጠቃሚነትን ለመዋጋት 3 ሚሊየን ዶላር ለመሰብሰብ ንቅናቄ አስጀመረች

ዚምባብዌ አደንዛዥ እፅ እና ሱስ ተጠቃሚነትን ለመዋጋት 3 ሚሊየን ዶላር ለመሰብሰብ ንቅናቄ አስጀመረች
በሃራሬ በተካሄደ የገንዘብ ማሰባሰብያ ንቅናቄ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የተደራጁ የውንብድና ቡድኖች እና ፍርደኛ ወንጀለኞችን ጨምሮ የአደንዛዥ እፅ ተከሳሾችን የሕግ አስከባሪ አካላት ለፍርድ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል፡፡
ምናንጋግዋ የዜጎች ጤና እና ደህንነት ለሀገራዊ ልማት እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ቁልፍ መሆኑን አስምረዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት መንግሥታቸው አደንዛዥ እፅ እና ሱስን የሚዋጋ ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም አጠቃላይ ኅብረተሰቡን ያማከለ አካሄድ እንደተከተለ ገልፀዋል።
ኮሚቴው ትኩረት የሚያደረግባቸው ሰባት ምሰሶዎችን ጠቅሰዋል፦
🟠 የአቅረቦት ቅነሳ፣
🟠 የፍላጎት ቅነሳ፣
🟠 የጉዳት ቅነሳ፣
🟠 ሕክምና እና ማገገም፣
🟠 የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፍ፣
🟠 ከማኅበረሰብ ዳግም ማቀላቀል፣
🟠 የሚዲያና ተግባቦት ስትራተጂዎች፣
ፕሬዝዳንቱ መሠረታዊ የሥልጠና እና የማገገሚያ ማዕከላት አስፈላጊነትን አጽንዖት በመሰጠት፤ አካባቢያዊ ባለሥልጣናት ለእነዚህ ተቋማት መሠረት ልማት እንዲያቀረቡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በመጨረሻም ምናንጋግዋ እና አስተዳደራቸው ለውጠኑ ቅድሚያ በመስጠት ከ2025 ብሔራዊ በጀት 7.8 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መመደቡን ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X