ሩሲያ በተባበሩት መንግሥታት የግብርና የወጪ ንግድ ስምምነት ውጤት ደስተኛ እንዳልሆነች ገለፀች
16:55 12.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 12.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በተባበሩት መንግሥታት የግብርና የወጪ ንግድ ስምምነት ውጤት ደስተኛ እንዳልሆነች ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በተባበሩት መንግሥታት የግብርና የወጪ ንግድ ስምምነት ውጤት ደስተኛ እንዳልሆነች ገለፀች
እ.ኤ.አ በ2022 በተባበሩት መንግሥታት-ሩሲያ ስምምነት መሠረት የሩሲያ እህል እና ማዳበሪያ ወደ ዓለም ገበያ ለመላክ የተቀመጡ አብዛኛዎቹ ኃላፊነቶች በምዕራባውያን ሀገራት አሉታዊ አቋም ምክንያት ተግባራዊ አልሆኑም ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ቬርሺኒን ቅዳሜ ተናግረዋል፡፡
"በርካታ የሩሲያ ኩባንያዎች ንብረቶች እገዳን ከማንሳት አንጻር ለውጦች እና መሻሻሎች አሉ፤ ይህም በሦስት ዓመታት የድርድር ሂደት ወቅት አፅዕኖት የሰጠንበት ነው" በማለት ነው ቬርሺኒን ለጋዜጠኞች የገለፁት፡፡
አሞኒያን ከሩሲያ ወደ ውጭ መላክ እና የግብርና ማሽነሪዎች መለዋወጫ ማስመጣትን ጨምሮ በመጪው ሐምሌ 15 ጊዜው በሚያበቃው ስምምነት ውስጥ ከተዘረዘሩት አምስት ተግባራት መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ ሙሉ በሙሉ አልተፈፀሙም ብለዋል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት የተጣሉት ማዕቀቦች የግብርና የወጪ ንግዶችን አይጎዳም በሚል የሚሰጠው መግለጫ ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ቬርሺኒን ማዕቀቡ እስያ፣ አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ ወዳሉ ታዳጊ ሀገራት የሚላከው የሩሲያ የግብርና ምርት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X