በስደተኞች ማቆያ አካባቢዎች 100 ሚሊየን ችግኞችን የመትክል የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውጥን
16:29 12.07.2025 (የተሻሻለ: 16:54 12.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበስደተኞች ማቆያ አካባቢዎች 100 ሚሊየን ችግኞችን የመትክል የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውጥን

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በስደተኞች ማቆያ አካባቢዎች 100 ሚሊየን ችግኞችን የመትክል የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውጥን
የዚሁ ንቅናቄ አካል የሆነው የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት እና የልማት አጋሮቹ በክረምቱ አምስት ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሥራ በጉለሌ እፅዋት ማዕከል በይፋ ተጀምሯል፡፡
ይህ ቁርጠኝነት በታህሳስ 2023 በጄኔቫ በተካሄደው የዓለምአቀፍ የስደተኞች ፎረም ወቅት ኢትዮጵያ በገባችው ቃል መሠረት በሚቀጥሉት አራት ዓመታት 100 ሚሊየን ሁለገብ ችግኞች በሁሉም የስደተኞች ካምፖች ዙሪያ ለመትከል ከገባችው ቃል የመነጨ ነው ተብሏል፡፡
እስካሁን በ26 የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች የተተከሉ ችግኞች የመፅደቅ ምጣኔ 85 በመቶ መድረሱም ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በማስተናገድ መሠረታዊ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰፊ ክብርና እውቅና እንዳገኘች ተጠቅሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X