የሳሕል ሀገራጥ ጥምረት ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ስብሰባ ረግጠው ወጡ

የሳሕል ሀገራጥ ጥምረት ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ስብሰባ ረግጠው ወጡ
የቡርኪና ፋሶ፣ የማሊ እና የኒጀር ልዑካን የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አርብ በቶጎ መዲና ሎሜ እያካሄደ ከነበረበት ክፍል ለቅቀው ወጥተዋል፡፡
ቡርኪና ፋሶ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የምክር ቤቱ ተለዋጭ ፕሬዝዳንት እንዳትሆን በመከለከሏ ምክንያት ስብስባውን መርገጣችውን ነው መገናኛ ብዙኃን የዘገቡት፡፡ በምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት መተዳደሪያ መሠረት ፕሬዝዳንቱ በአባል ሀገራቱ የገንዘብ ሚኒስትሮች ፈረቃ የሚያዝ እንደመሆኑ ውሳኔው የቡርኪና ፋሶን ሉዓላዊነት እንደመካድ ተቆጥሯል፡፡
ቡርኪና ፋሶ የሚገባትን የፕሬዝዳንትነት ቦታ እንዳታገኝ መከልከሏ በሕብረቱ አንድነት ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ተወስዷል፡፡ ክስተቱን ተከትሎ የሳሕል ሀገራጥ ጥምረት ተወካዮች በወደፊት ስብሰባዎች ሙሉ በሙሉ መሳተፋቸውን ለማቆም እና የሕብረቱ የአስተዳደር ሕጎች እንዲከለሱ መጠየቃቸው ነው የተዘገበው፡፡
በመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች የተጠቀሰ አንድ የማይታወቅ ምንጭ እንደገለጸው፤ ምንም እንኳን ፈረንሳይ የሲኤፍኤ ፍራንክ ዋስ ብትሆንም፤ ቡርኪና ፋሶ በባማኮ እና በኒያሚ ተደግፋ ከፈረንሳይ ጋር በገንዘብ ጉዳዮች ላይ ለመሥራት ፈቃደኛ አይደለችም፡፡ ይህ አለመግባባት አሁን በምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት የሀገር እና የመንግሥት መሪዎች ጉባኤ ሊፈታ ይችላል የሚል ተስፋ ተጥሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X