የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግብይት መጀመሩ የሀገሪቱን የሪፎርም ሥራ እንደሚያጠናክር የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግብይት መጀመሩ የሀገሪቱን የሪፎርም ሥራ እንደሚያጠናክር የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተናገሩ
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግብይት መጀመሩ የሀገሪቱን የሪፎርም ሥራ እንደሚያጠናክር የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.07.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግብይት መጀመሩ የሀገሪቱን የሪፎርም ሥራ እንደሚያጠናክር የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተናገሩ

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ትናንት በይፋ ግብይት ጀመሯል። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ቁጥጥር በሚደረግበት የገበያ ሥርዓት የሁለቱ ማለትም የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶች እና የግል የድርሻ ግብይትን ያስጀመረችበት ነው፡፡

ሚኒስትር አህመድ ሽዴ “የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶች የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያዎች እንዲመዘገቡና እንዲገበያዩ መደረጉ የሪፎርም ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር ይረዳል” ብለዋል።

የገበያው ዋና ዓላማ ውጤታማ የካፒታል ማሰባሰብ ሥራዎችን በማጠናከር የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት እድገት ግልጽና ደህንነቱ በተጠበቀ የካፒታል ገበያ ሥራዎች መደገፍ እንደሆነ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልኩ “የገበያው መጀመር ኢትዮጵያ በሀገር በቀል ምጣኔ ሃብት ማሻሻያው እያከናወነች ባለው ሁሉን አቀፍ ጠንካራና ገበያ መር ምጣኔ ሃብት ግንባታ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው” ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0