ማሌዥያ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ስትል ከሰሰች
20:00 11.07.2025 (የተሻሻለ: 20:04 11.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱማሌዥያ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ስትል ከሰሰች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማሌዥያ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ስትል ከሰሰች
"በፍልስጤም ግዛት በዘመናዊ ታሪክ ረጅሙ ጦርነት እና መሠረቱን ኢፍትሐዊና ሕገወጥ ወረራ ላይ ያደረገው ግጭት ሊቆም ይገባል" ሲሉ የማሌዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሀሰን በምስራቅ እስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
ሀሰን አክለውም "ለሰማንያ ዓመት ከተጠያቂነት ውጪ ሆና የቆየችው እስራኤል ጨቅላ ህፃናትንና ልጆችን ጨምሮ የጅምላ ረሃብና ግልፅ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንድትፈጽም ተበረታትታለች" ብለዋል።
እ.ኤ.አ በታህሳስ 2023 ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች በሚል በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት ክስ መስርታ ነበር። በግንቦት 2024 ፍርድ ቤቱ እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ የምትፈፅመውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆም እና የምርመራ ልዑካን ወደ ጋዛ እንዲገቡ እንድትፈቅድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
እ.አ.አ በህዳር 2024 የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በጋዛ ውስጥ የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በመጥቀስ፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ እንዳወጣ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X