- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

"የሌማት ትሩፋት"፦ የኢትዮጵያ የውስጥ አቅምና ዕውቀት ለምግብ ሉዓላዊነት

"የሌማት ትሩፋት"፦ የኢትዮጵያ የውስጥ አቅምና ዕውቀት ለምግብ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
እ.ኤ.አ በ2022 የተጀመረው የሌማት ትሩፋት፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት ለመቀየር መንግስት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ኢኒቬቲቭ ነው።
ኢኒሼቲቩ የወተት፣ የዶሮ እርባታ፣ የማርና የአሳ ምርትን እያሳደገ፣ አምራቾችን እያበረታታ እንዲሁም እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱን ምግብ እንዲያመርት፣ በአካባቢ ገበያዎች እንዲሳተፍ እያደረገ ስለመሆኑም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ዉጥን ከግብ ለማድረስም አጋዥ ነው ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)
“በእርግጥም ከአቅርቦት እጥረት ወደ ትርፍ ምርት የሚያተኩር ተነሳሽነት አለን […] ስለዚህ በውጭ እርዳታ ላይ ያለው ጥገኝነት ሊቀንስ ይችላል።” በማለት ተናግረዋል፡
ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የብሪክስ ጥምረትም ሀገሪቱ በቀጣይ ለሰነቀችው ዓለም አቀፍ የገበያ ትስስር ከወዲሁ ተስፋ መሆን ችሏል።
“የእኛ የብሪክስ አባልነት ገበያዎችን እንድንጠቀም ሊረዳን ይችላል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርም ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ መድረክ ልታመጣቸው ከምትችላቸው አጀንዳዎች አንዱ ሊሆን ይችላል።” ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የሀገር በቀል እውቀት + ዓለም አቀፍ ህብረት = ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን የምታረጋግጥበት መንገድ
ሃሳቡን በጥልቀት ለመረዳት ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን የራይዚንግ ሳውዝ ፕሮግራም ይከታተሉ!
አዳዲስ ዜናዎች
0