የሩሲያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር የስፑትኒክ ጋዜጠኞች እስርን አስመልክቶ ከአዘርባጃን እንባ ጠባቂ ጋር እንደተነጋገሩ አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር የስፑትኒክ ጋዜጠኞች እስርን አስመልክቶ ከአዘርባጃን እንባ ጠባቂ ጋር እንደተነጋገሩ አስታወቁ
የሩሲያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር የስፑትኒክ ጋዜጠኞች እስርን አስመልክቶ ከአዘርባጃን እንባ ጠባቂ ጋር እንደተነጋገሩ አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.07.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር የስፑትኒክ ጋዜጠኞች እስርን አስመልክቶ ከአዘርባጃን እንባ ጠባቂ ጋር እንደተነጋገሩ አስታወቁ

ታቲያና ሞስካልኮቫ እንባ ጠባቂው ሳቢና አሊዬቫ "ፍትሕ እና ሕጋዊነትን ለማስፈን በተቻላቸው አቅም አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ መጠየቃቸውን" ለስፑትኒክ ገልፀዋል። አክለውም አቤቱታው ተቀባይነት እንዳገኛ እና መረጃውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ መግለፃቸውን አስታውቀዋል።

"ዜጎቻችን ራሳቸው የመረጧቸው ጠበቆች እንዲቆሙላቸው እና የተሟላ የቆንስላ ድጋፍ ማግኘታቸው በጣም አስፈላጊ ነው" ብለዋል ሞስካልኮቫ።

የአዘርባጃን ባለሥልጣናት ሰኔ 23 በስፑትኒክ አዘርባጃን ኤጀንሲ ሰባት ሠራተኞችን ያለበቂ ምክንያት አስረዋል። የኤዲቶሪያል ቢሮ ኃላፊ እና ዋና አዘጋጅ የአራት ወራት እስር ተላልፎባቸዋል።

የስፑትኒክ አካል የሆነው ሮሲያ ሴጎድኒያ የሚዲያ ቡድን የአዘርባጃን ሕግ አስከባሪዎችን ድርጊት መሠረተ ቢስ በማለት፤ ክሱ ከእውነት የራቀ እንደሆነ አስታውቋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ባኩ የስፑትኒክ አዘርባጃን ጽህፈት ቤትም ሆነ የጋዜጠኞቹን ሥራ በተመለከተ ምንም አይነት አቤቱታ አቅርባ እንደማታወቅ ቀደም ብለው ተናግረዋል። በኤጀንሲው ላይ የተወሰዱ ርምጃዎች ከሌሎች ጉዳዮች ጋር የተያያዙ እንደሆነም ነበር የጠቆሙት።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0