ትጥቅ የፈቱ የኩርዲስታን የሠራተኞች ፓርቲ አባላት የጦር መሳሪያዎቻቸውን አቃጠሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትጥቅ የፈቱ የኩርዲስታን የሠራተኞች ፓርቲ አባላት የጦር መሳሪያዎቻቸውን አቃጠሉ
ትጥቅ የፈቱ የኩርዲስታን የሠራተኞች ፓርቲ አባላት የጦር መሳሪያዎቻቸውን አቃጠሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.07.2025
ሰብስክራይብ

ትጥቅ የፈቱ የኩርዲስታን የሠራተኞች ፓርቲ አባላት የጦር መሳሪያዎቻቸውን አቃጠሉ

በቱርክ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የኩርዲስታን ሠራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) በደርዘን የሚቆጠሩ አባላት በሰሜናዊ ኢራቅ የጦር መሳሪያዎቻቸውን በይፋ አቃጥለዋል።

እርምጃው በዋነኝነት በደቡብ ምስራቅ ቱርክ፣ በሰሜን ኢራቅ እና በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ የኩርድ ማሕበረሰቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች መሠረቱን ያደረገው ቡድን ትጥቅ የማስፈታት ሂደት ትልቅ ምዕራፍ ነው።

ይህም ባለፈው ግንቦት ፒኬኬ መፍረሱን እና ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ከቱርክ ጋር ሲያካሂድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ለማቆም መወሰኑን ተከትሎ የመጣ ነው። እንደ ስፑትኒክ ምንጭ ከሆነ የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ ሁለተኛ ምዕራፍ በሚቀጥሉት ቀናት ይቀጥላል።

ፒኬኬ እ.ኤ.አ በ1978 በቱርክ የሚኖሩ የኩርድ ሕዝቦችን መብት ለማስጠበቅ እነደተመሠረተ የሚገልፅ ሲሆን አንካራ ግን በሽብር ድርጅትነት ፈርጃዋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0