ናይጄሪያ አሜሪካ የቬንዙዌላ ስደተኞችን እንዲቀበሉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የምታደርገውን ግፊት ተቃወመች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ አሜሪካ የቬንዙዌላ ስደተኞችን እንዲቀበሉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የምታደርገውን ግፊት ተቃወመች
ናይጄሪያ አሜሪካ የቬንዙዌላ ስደተኞችን እንዲቀበሉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የምታደርገውን ግፊት ተቃወመች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.07.2025
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ አሜሪካ የቬንዙዌላ ስደተኞችን እንዲቀበሉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የምታደርገውን ግፊት ተቃወመች

"አሜሪካ ከሀገሪቷ የምታባርራቸውን የቬንዙዌላ ስደተኞች እና ከእስር ቤት በቀጥታ የሚተላለፉ እስረኞችን የአፍሪካ ሀገራት እንዲቀበሉ ከፍተኛ ጫና እያደረገች ነው" ሲሉ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ቱጋር በብራዚል ከተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ናይጄሪያ 230 ሚሊየን ሕዝብ እንዳላት በመጥቀስ "እንደ ናይጄሪያ ላለች ሀገር የቬንዙዌላን እስረኞች መቀበል ከባድ ይሆናል፤ የራሳችን ችግሮች አሉብን" ብለዋል።

ንግግሩ በቅርቡ በኋይት ሃውስ በተካሄደው ስብሰባ የላይቤሪያ፣ ሴኔጋል፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ሞሪታኒያ እና ጋቦን መሪዎች ከአሜሪካ የሚባረሩ የሌላ ሀገር ስደተኞችን እንዲቀበሉ መጠየቁን ተከትሎ የመጣ ነው።

ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ የእነዚህን የሶስተኛ ሀገር ዜጎች "በክብር፣ በደህንነት እና በወቅቱ ማዛወርን" እንደሚጠይቅ ተገልጿል።

ትራምፕ ስደተኞችን ከአሜሪካ የማስወጣት ሂደቱ እንዲፋጠን ግፊት እያደርጉ ሲሆን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሂደት ሲስተጓጎል ወደ ሶስተኛ ሀገራት እንዲዛወሩም እየጠየቁ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0