የትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩነት እና የጦር መሳሪያ ሽያጭ ግፊታቸው “እርስ በእርሱ ይቃረናል” ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩነት እና የጦር መሳሪያ ሽያጭ ግፊታቸው “እርስ በእርሱ ይቃረናል” ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ
የትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩነት እና የጦር መሳሪያ ሽያጭ ግፊታቸው “እርስ በእርሱ ይቃረናል” ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.07.2025
ሰብስክራይብ

የትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩነት እና የጦር መሳሪያ ሽያጭ ግፊታቸው “እርስ በእርሱ ይቃረናል” ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ

የብሪክስ የምርምር ተቋም ኃላፊ ፕሮፌሰር ፉሉ ኔትስዌራ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሴኔጋል፣ ላይቤሪያ፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ጋቦን እና ሞሪታኒያ የሰጡትን የፀረ-ሽብር አመክንዮ፤ በሀገራቱ ውስጥ ዝቅተኛ የሽብርተኝነት ስጋት መኖሩን በመጥቀስ ልክ እንዳልሆነ ሞግተዋል።

ኔትስዌራ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ይህንን ፖሊሲ ስውር ማስፈራሪያ ሊሆን እንደሚችል በማንሳት፤ የጦር መሳሪያዎችን ከአሜሪካ አለመግዛት በማንኛውም ጊዜ በሀገራቱ ሁከትን ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።

አክለውም ወታደራዊ ወጪን መጨምር የሀገራቱ የኢኮኖሚ ልማት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር፣ ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ እንደሚዘፍቃቸው እና ገንዘቡ ወሳኝ በሆኑ ፍላጎቶች ላይ እንዳይውል ሊያደርግ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

"ይህ እጅግ ከፍተኛ ጥፋት ነው...ለአሜሪካ ታዛዥ ሆነው ይቀጥላሉ [...] በዚህም የኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ሉዓላዊነት ጉዳይ ወደ ጎን ይባላል" ሲሉ ተናግረዋል።

የአሜሪካ አስተዳደርን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ግፊት ግዙፍ የጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያዎች በዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲካ ላይ ከሚያሳድሩት ተፅዕኖ ጋር ያገናኙት ባለሙያው፤ የአፍሪካ ሀገራት ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0