መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመጪው መስከረም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እንደሚጀመር ተገለፀ
14:06 11.07.2025 (የተሻሻለ: 14:14 11.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመጪው መስከረም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እንደሚጀመር ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመጪው መስከረም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እንደሚጀመር ተገለፀ
በቅድሚያ በአዲስ አበባ የተጀመረው አገልግሎቱ 23 ተቋማትን በማዋሃድ 120 የሚሆኑ አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር እያቀረበ ይገኛል።
መሶብ ድሬዳዋን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ አስታውቀዋል።
አክለውም የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ በመደገፍ እንግልትን በመቀነስ ረገድ ውጤት ማሳየቱን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X