ኢትዮጵያ ቪዛቸውን አሳልፈው የሚቆዩ የውጭ ዜጎችን አስጠነቀቀች
12:09 11.07.2025 (የተሻሻለ: 12:14 11.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ቪዛቸውን አሳልፈው የሚቆዩ የውጭ ዜጎችን አስጠነቀቀች
ማሳሰቢያው አሜሪካ ለኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ካሜሩን ዜጎች የሚሰጠው የቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን ማስታወቋን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የውጭ ዜጎች በተለይም የአሜሪካ ፓስፖርት ለያዙቱ፤ ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ መቆየት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት እንደሚያስቀጣቸው አሳስበዋል።
ከዚህ በፊት ኢትዮጵያውያን ዜጎች በተለይም ለንግድ እና ቱሪዝም ወደ አሜሪካ የሚጓዙ አመልካቾች ለሁለት ዓመት የሚቆይ ቪዛ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ከሐምሌ 2 ጀምሮ ግን ለ3 ወር የሚቆይ የአንድ ግዜ መግቢያ ቪዛ መስጠት እንደሚጀምር አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X