"አዲስ ነገር ጠብቁ"፦ ላቭሮቭ ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ አዲስ አቀራረብ ትከተላለች አሉ
11:16 11.07.2025 (የተሻሻለ: 11:24 11.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"አዲስ ነገር ጠብቁ"፦ ላቭሮቭ ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ አዲስ አቀራረብ ትከተላለች አሉ
ትራምፕ በቅርቡ አዲስ ዜና ጠብቁ ማለታቸውን እየጠቀሱ እንደሆነ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
ትናንት ከላቭሮቭ ጋር የተገናኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዋሽንግተን በዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት አዳዲስ ሀሳቦችን እንደተቀበለች ገልጸዋል።
ላቭሮቭ ከደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ማህበር ጉባኤ ጎን ለጎን ከሩቢዮ ጋር ባደረጉት ውይይት ሩሲያ በዩክሬን ዙሪያ የያዘችውን አቋም በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል። አክለውም አዲሱ ስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት በድርድራቸው ወቅት የመነጋገሪያ ርዕስ እንዳልነበረ ግልጽ አድርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X